ፈልግ

እኛ ማነን?

የቫቲካን ኒውስ የቫቲካን ሬዲዮ ፣ ኦዜርቫቶሬ ሮማኖ እና የቫቲካን ሚዲያዎች በጋራ በወቅታዊው ባህል ውስጥ “ለቤተክርስቲያኗ ተልዕኮ ፍላጎቶች በተሻለ ሁኔታ” ምላሽ ለመስጠት በማቀድ የሚተላለፍ የቅድስት መንበር የመረጃ መስጫ ተቋም ነው። የቫቲካን ኒውስ እ.አ.አ. በሰኔ 27/ 2015 ዓ.ም ላይ በርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቼስኮስ የግል ተነሳሽነት በቅድስት መንበር ሥር የሚተዳደር አዲስ የመገናኛ ብዙዐን ጽሕፈት ቤት እንዲመሰረት ባወጁት አዋጅ መሰረት የተቋቋመ ሲሆን ዛሬ ደግሞ የጳጳሳዊ ጉዳዮችን በሚያስተዳድረው ጽሕፈት ቤት ሥር የሚተዳደር ተቋም ነው።

የቫቲካን ኒውስ ከእዚህ ቀደም ይጠቀምባቸው የነበረውን ቀለል ያለ ዲጂታል የመገናኘት ፅንሰ-ሀሳብን በመሻገር  ምላሽ ለመስጠት እና በተወሰነ መልኩም ቢሆን በመገናኛ አውታሮች እና ቅርፅ ላይ በተከታታይ እየተከሰተ ባለው ቀጣይነት ያላቸው ለውጦችን ከግምት ባስገባ መልኩ በልዩ ልዩ ባህሎች ውስጥ “የምህረትን ወንጌል ለሁሉም ህዝቦች ለማድረስ” ዓላማ ያነገበ ተቋም ነው። ይህ ተቋም ሥራውን በማከናወን ራሱን የሚገልጸው በድምፅ ፣ በቪዲዮ ፣ በፅሁፍ ፣ በምስል ፣ በታገዘ መልኩ በብዙ ቋንቋዎች፣ በብዙ የተለያዩ ባሕሎች፣ በብዙ አውታሮች፣ በመልቲሚዲያ እና በብዙ መሣሪያዎች በመታገዝ  ነው።

የርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፣ የቅድስት መንበር ፣ የአጥቢያ አብያተ ክርስቲያናት እንቅስቃሴ እንዲሁም ከዓለም ዙሪያ የተገኙ መረጃዎች የሚያቀርቡበት አራት ክፍሎች አሉት። የቫቲካን ኒውስ በቫቲካን ሬዲዮ የቋንቋ ኤዲቶሪያል ጽህፈት ቤቶች የአሠራር ጥንካሬ ላይ የተመሠረተ ነው (የቫቲካን ሬዲዮ ስርጭት በጉሌልሞ ማርኮኒ ሐሳብ አምንጪነት የተነደፈ እና የተገነባ፣ በርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፒየስ 16 ኛ ተመርቆ እ.አ.አ በየካቲት 12 ቀን 1931 ዓ.ም ሥራውን በይፋ መጀመሩ ይታወሳል) የተመሰረተውም መረጃዎችን ለማቅረብ ብቻ ታስቦ ሳይሆን በዓለም ዙሪያ የእምነት ተስፋን ለማምጣት እና እውነታዎችን በቅዱስ ወንጌል የአተረጓጎም ቁልፍ በመጠቀም ማቅረብ ነው።  የመመሪያው መስፈርት "ሐዋርያዊ  እና ሚስዮናዊ ነው ፣ ለመከራዎች፣ ለድህነት ፣ አስቸጋሪ ለሆኑ ሁኔታዎች ልዩ ትኩረት ይሰጣል" (ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ ለኮሙኒኬሽን ጽሕፈት ቤት ምልዓተ-ጉባ እ.አ.አ በግንቦት 4 ቀን 2017 ዓ.ም ካደረጉት ንግግር የተወሰድ) ፡፡

ዋና አስተዳደር
ፓውሎ ሩፊኒ

የኤዲቶሪያል ዳይሬክተር
አንድሪያ ቶርኒሊ

ምክትል ዳይሬክተሮች
ሰርጆ ቼንቶፋንቲ - አሌሳንድሮ ጂዞቲ

የቫቲካን ራዲዮ እና የቫቲካን ኒውስ ኃላፊ
ማሲሚላኖ ማኒኬቲ